Fana: At a Speed of Life!

አውስትራሊያ ከወራት በፊት ተቀስቅሶ በነበረው ሰደድ እሳት ጉዳይ ላይ ምርመራ ጀመረች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አውስትራሊያ ባለፈው መስከረም ወር ተቀስቅሶ በነበረው ሰደድ እሳት ጉዳይ ላይ ምርመራ ጀመረች።

የሰደድ እሳት ጉዳዮችን የሚመለከተው ኮሚሽንም ረጅም ጊዜ የሚወስደውን ምርመራ በዛሬው እለተ መጀመሩን አስታውቋል።

በምርመራው የደረሰው አጠቃላይ ጉዳት፣ የነበረው ምላሽ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ይዳሰሳሉ ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ወደፊት ሊከሰቱ ለሚችሉ መሰል አደጋዎች ያለው ዝግጁነትና ምላሽ ምን መሆን አለበት የሚለው ጉዳይም የምርመራው አካል መሆኑ ተገልጿል።

መስከረም ወር ላይ ጀምሮ ለወራት የዘለቀው ሰደድ እሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የዱር እንሳስትን ህይዎት ቀጥፏል።

ከዚህ በተጨማሪም 34 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 2 ሺህ 800 ቤቶች ደግሞ ወድመዋል።

በአጠቃላይም 18 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በሰደድ እሳቱ ሲወድም ከ110 ቢሊየን ዶላር በላይ ኢኮኖሚያዊ ጉዳትም አስከትሏል ነው የተባለው።

አሁን ላይ በሰደድ እሳቱ የተጎዳው መሬት መልሶ እንዲያገግም የሚደረገው ጥረትም፥ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ ችግር ገጥሞታልም እየተባለ ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ እና አልጀዚራ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.