Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ለደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ አውሮፕላን እና አብራሪዎችን ለማቅረብ ፈቃደኛ ነው – አቶ ተወልደ

አዲስ አበባ ፣መስከረም 25 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን፣ አብራሪዎች ለማቅረብና እና የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማሪያም ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ጋር በሚፈፀም የሽርክና ስምምነት ለሀገሪቱ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን፣ አብራሪዎች በማቅረብ የጥገና አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የኦፕሬሽናል ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችላቸውን መንገድ እየተመለከቱ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው ብድር መክፈል እና ለሰራተኞች የሚደረግን ወጪ መቀነስ በተመለከተ ግን ፍላጎት እንደሌላቸው ተናገረዋል።

የውርስ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ማድረግ እንፈልጋለን ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሲሆን የብድር፣ የሰራተኞች ጉዳይ እና ሌሎች ስራዎች ለእኛ ከባድ የሚሆኑት ከገንዘብ አንፃር ብቻ ሳይሆን መዋቅሩን ከማስተዳደር ጋር ተያይዞ ነው ብለዋል።

አውሮላኖችን፣ ባለሙያዎችን፣ አብራሪዎችን፣ ቴክኒሻኖችን እና የአመራርነት አገልግሎት በማቅረብ ለደቡብ አፍሪካ አየር መንገድ በረራ የመጀመር ስራን ቀላል ማድረግ እንፈልጋለን ሲሉም ለብሉምበርግ ገልፀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.