Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ያቋረጠውን የናይጄሪያ – ኢኑጉ በረራ ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ናይጄሪያ ኢኑጉ ከተማ የድጋሚ በረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ናይጄሪያ ቢሮ ሀላፊ ሽመልስ አራጌ አስታወቁ፡፡

አየር መንገዱ የድጋ በረራውን ከመስከረም 21 ቀን ጀምሮ ሲጀምር ቦይንግ 787 አውሮፕላንን እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡

ወደ ከተማዋ የሚደረገው በረራ በሳምንት ሶስት ቀናት ማለትም ዘወትር ረቡዕ፣ አርብ እና ቅዳሜ መሆኑን ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡

መስከረም 21 ቀን ናይጄሪያ ከቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችበት ቀን በመሆኑ÷ በዚህ የነጻነት ቀን ወደ ኢኑጉ ከተማ በረራ መጀመር ደግሞ አሁንም በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል የነበረውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክረዋል ብለዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም አየር መንገዱ ወደ ኢኑጉ ከተማ ሲያደርግ የነበረውን በረራ እኤአ በ2019 ያቋረጠው የናይጄሪያ የበረራ ባለስልጣን አየር መንገዱን ለጥገና መዝጋቱን ተከትሎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

የኢኑጉ ከተማ አየር መንገድ ለጥገና ከመዘጋቱ በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከተማዋ ዓለም አቀፍ በረራ የሚያደርግ ብቸኛው አየር መንገድ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ አየር መንገዱ እኤአ በ2020 የሀገር ውስጥ በረራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ እንዲሁም እኤአ ነሀሴ 2021 የዓለም አቀፍ በረራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ተከትሎ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ከተማዋ ለመብረር የተዘጋጀው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.