Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ወርሃዊ ወጪውን ሸፍኖ ለሀገር ኢኮኖሚውም ድጋፍ እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ120 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማስገባት ወርሃዊ ወጪውን ሸፍኖ ለአገር ኢኮኖሚ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ዋና ሥራአስፈጻሚው ተናገሩ።

ዋና ሥራአስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደተናገሩት፥ አየር መንገዱ ፈጥኖ ወደ ካርጎ አገልግሎት መግባቱ  ውጤታማ አድርጎታል።

ኮቪድ- 19 በዓለም ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ በአየር መንገዱ ላይም ተመሣሣይ ጉዳት ማድረሱን ገልጸው፤ በርካታ አየር መንገዶች በድጎማና በብድር ውስጥ በገቡበት ወቅት አየር መንገዱ ወጪውን ሸፍኖ ለመንግሥት ድጋፍ ለማድረግ በቅቷል ብለዋል።

ለውጤታማነቱ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የኮቪድ- 19 መከላከያ ቁሳቁስ የሚተላለፍባት ምቹ ቦታ ተደርጋ መወሰዷና አየር መንገድ በዓለም ገበያ ላይ አበባ ለማጓጓዝ ተመራጭ እንዳደረገው አመልክተዋል።

አየር መንገዱ በቀን ከ200 እስከ 300 ቶን አበባ ወደ ተለያዩ አገሮች በማጓጓዝ በኢትየጵያ ያለውን የአበባ ምርት እንዲበረታታና በውጭ ምንዛሪ ኢኮኖሚውን እየደገፈ ነው ብለዋል።

በረመዳን ወቅት ሥጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በማጓጓዝ ገቢ ማግኘቱን ዋና ሥራአስፈጻሚው አብራርተዋል።

አየር መንገዱ ወጪውን ሸፍኖ ለአገሪቱ ኢኮኖሚው ድጋፍ ማድረጉ በዓለም ካሉት አየር መንገዶች ጠንካራ ያስብለዋል ብለዋል።

በቀጣይም የዓለም አቀፉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማየት ተጨማሪ የመንገደኛ አውሮፕላኖችን ወደ ጭነት ማመላለሻነት ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ተወልደ አስታውቀዋል።

የአየር መንገዱ 90 በመቶ የመንገደኞች አውሮፕላኖች የኮሮና ቫይረስ ባመጣው ተፅዕኖ ምክንያት ሥራ ማቆማቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.