Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማጓጓዝ ዝግጅት አጠናቋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማጓጓዝ ዝግጅቱን አጠናቆ ክትባቱ ለትራንስፖርት ዝግጁ እስከሚሆን ድረስ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።
ክትባቱን ለማጓጓዝም የአሊባባው ሳይናው ግሎባል ድርጅት ጋር በአጋርነት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የአየር መንገዱ መረጃ የሚያመለክተው።
ክትባቱ ደረጃውን በጠበቀ ማቀዝቀዣ ተቀምጦ በሣምንት ሁለት ጊዜ ከሼንዘን ወደ አፍሪካ፤ እንዲሁም በአዲስ አበባና በዱባይ አድርጎ ለመላው ዓለም እንደሚሰራጭ ተገልጿል።
ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር በቻይና የመድኃኒት ሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲሰጡ ፈቃድ ከሰጣቸው አራት አውሮፕላን ማረፊያዎች የሼንዘን አውሮፕላን ማረፊያ አንዱ ነው።
ኬኒዎስ ስማርት ሎጂስቲክስ ኔትወርክ የአሊባባ ግሩፕ አካል ሲሆን፥ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር የመድኃኒት ማጓጓዝ አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
በቻይና የመጀመሪያ የሆነው ድንበር ተሻጋሪ የመድኃኒት ማጓጓዝ አገልግሎት በመደበኛነት የሚተገበር ሲሆን፥ የኮቪድ-19 ክትባትን ጨምሮ የማቀዝቀዣ ቁጥጥርን በመተግበር ሌሎችን መድኃኒቶች ለማጓጓዝ ፈቃድ ተሰጥቶታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ተርሚናል ባለው ማቀዝቀዣና መሰል አገልግሎት መስጫዎች ለስራው ብቁ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም “አየር መንገዱ የተጎናጸፈውን አኩሪና ዓለም አቀፋዊ ስኬት መሰረት በማድረግ ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ የኮቪድ-19 የግል መከላከያ ቁሳቁሶችን ማጓጓዙን አስታውሰዋል።
“አሁንም ባገኘው ስኬት በመታገዝ የኮቪድ-19 ክትባትን ለመላው ዓለም ያሰራጫል” ያሉት አቶ ተወልደ፤ “የኮቪድ-19 ክትባት መሰራጨት ሲጀመር ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ግንባር ቀደም በመሆን ክትባቱ ለመላው ዓለም እንዲዳረስ እናደርጋለን” ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.