Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የኮቪድ19 ክትባትን ዓለም ላይ ለማሰራጨት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮቪድ19 ክትባትን ዓለም ላይ ለማሰራጨት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ዓለም ላይ ያለው የኮቪድ19 ክትባት ፍላጎት እስከ ሦስት ዓመታት ሊዘልቅ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወረርሽኙ ሳቢያ የተጓዦች ቁጥር ቢቀንስበትም አውሮፕላኖችን የጭነት አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ በገቢ ላይ ይደርስ የነበረውን ተፅዕኖ መቋቋም ችሏል፡፡

የአየር መንገዱ የካርጎ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍፁም አባዲ የአየር መንገዱ ዋነኛ ደንበኞች የሃገራት ጤና ሚኒስትሮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አየር መንገዱ ትናንት ማለዳ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን መጠን የኮሮና ቫይረስ ክትባት ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡

የተጓዦች ቁጥር በአሁኑ ወቅት እያንሰራራ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ ፍጹም ከመደበኛ ወቅት አንጻር ሲታይ በአሁኑ ወቅት ግማሽ የሚሆኑትን ማስተናገድ መጀመሩን ለሬውተርስ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.