Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ የኮቪድ19 ክትባት ወደ ብራዚል አጓጓዘ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን የኮቪድ19 ክትባት ከሻንጋይ ወደ ብራዚል ሳኦ ፖሎ አጓጓዘ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደገለፁት፥ አየር መንገዱ የኮቪድ19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የሚደረገውን የመከላከል ጥረት ለማገዝ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ወረርሽኙን ለመመከት በሚደረገው ጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ በክትባት ስርጭቱ አየር መንገዱ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላኖችን ወደ እቃ ጫኝነት በመቀየር የሚሰጠውን የጭነት አገልግሎት አሳድጓል፡፡

አየር መንገዱ እስካሁን ድረስ ከ20 ሚሊየን በላይ የኮቪድ19 ክትባቶች ከ20 በላይ ወደሆኑ ሃገራት አጓጉዟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.