Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ተመራጭ  የማላዊ  ፕሬዝዳንት ቃለ መሃላ ፈጸሙ

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 21 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የማላዊ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ላዛሩስ ቻክዌራ በማላዊ እንደገና በተካሄደው ፕሬዚንደንታዊ ምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ዛሬ  ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

ላዛሩስ ማክሰኞ ዕለት በተካሄደው በዚህ ምርጫ 58 ነጥብ 57 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሁን በሥልጣን ላይ ያሉትን ተፎካካሪያቸውን ፒተር ሙታሪካን ማሸነፋቸው ተነግሯል።

ፒተር ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በተካሄደው ምርጫ እንዳሸነፉ ተገልጾ ነበር÷ ይህንን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ  ከመነሳቱም ባለፈ  ላዛሩስም ምርጫው ፍትሃዊ እንዳልሆነ በመግለጽ ለፍርድ ቤት አቤት ብለው ነበር፡፡

ጉዳዩን ሲያይ ነበረው የአገሪቷ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤትም ፒተር ያሸነፉት “በድምጽ ማጭበርበር” እንደሆነ በመግለጽ ያሳለፍነው የካቲት ወር ላይ ውጤቱ ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቋል፡፡

ይህንን ተከትሎም ባሳለፍነው ሳምንት በአገሪቱ ድጋሜ ምርጫ ተካሂዷል

በዚህም ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ መሪው ላዛሩስ ቻክዌራ ማሸነፋቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

የዚህ ምርጫ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ላዛሩስ፤ “ድሌ ለዲሞክራሲና ለፍትህ ነው” ሲሉ በማሸነፋቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ደጋፊዎቻቸውም በመዲናዋ ሊሎንግዌ አደባባይ በመውጣት ርችት በመተኮስና የመኪና ጡሩምባ በማሰማት ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ማላዊ በኬንያ በፈረንጆቹ 2017 ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ከተሰረዘ በኋላ  ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተሰረዘባት ሁለተኛዋ አፍሪካዊ አገር ሆናለች ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.