Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች አማካኝነት የቀረበ 50 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ አዲስ አበባ ለሚገኙ ሲሚንቶ ፈላጊዎች ከ377 ብር በታች እንዲሸጥ መወሰኑን የንግድን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም ደርባ 343 ብር ከ35፣ ሙገር 352 ብር ከ63፣ ሐበሻ 364 ብር ከ39 እና 376 ብር ከ28 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ በሲሚንቶና ሌሎች ምርቶች ላይ የሚስተዋለው ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሕገ ወጥ ደላሎች እና ሌሎች የፖለቲካ አሻጥረኞች በሚሠሩት ሴራ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማሻሻል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፥ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ሚናው ከፍተኛ ለሆነው የግንባታው ዘርፍ በዋና ግብዓትነት የሚያገለግለውን የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት ስርዓትና የዋጋ መጨመር ለማስተካከል እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም የስርጭት ፍትሐዊነቱን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለኅብረተሰቡ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተወስኗል ነው ያሉት፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.