Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከፍተኛ ሊግ ውድድሩን ሲያርግ የቆየው አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

አዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ19ኛ ሳምንት ከኢኮሥኮ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 0 በማሸነፍ ነው ማለፉን ያረጋገጠው።

በዚህም ነጥቡን 48 ያደረሰ ሲሆን ሦስት ጨዋታዎች እየቀሩት ወደ 2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ክለብ ወደ ኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ማለፉን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

“የአዲስ አበባ እግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው እለት ማለፉን አረጋግጧል ፤ እንኳን ደስ አለን” ሲሉ መግለፃቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.