Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀንና በማታ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 87 ተማሪዎቹን አስመረቀ::
የምረቃ ስነስርዓቱ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ዛሬ የተመረቃችሁ ተማሪዎች የሕይወታችሁን አዲስ ምዕራፍ ጀምራችኋል፤ ኢትዮጵያን ነገ የምትመሯት፣ የምታስተዳድሯት፣ የምትታገሉላት፣ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትወክሏት እናንተ ናችሁ ብለዋል።
በየቦታው የሚሰማው እና የሚታየው አሰቃቂ ነገር ኢትዮጵያን የሚያኮስስ እና የሚያሸማቅቅ ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መፃኢው የኢትዮጵያ ተስፋ ብሩህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ኢትዮጵያ ሁሉንም ልጆቿን የምትሻበት ጊዜ ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ተማሪዎች የተለየዩ መሰናክሎችን አልፈው ለምረቃ መብቃታቸውን ገልፀዋል፡፡
ዛሬ ከተመረቁት ተማሪዎች መሀካከል 2 ሺህ 635 ወንዶች ሲሆኑ 1 ሺህ 452 ተማሪዎች ደግሞ ሴቶች ናቸው።
ከተመራቂዎቹ መሀከል 48ቱ በ3ኛ ዲግሪ በቀን ያሰለጠናቸው ናቸው።
በ2012/2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የዛሬውን ተመራቂዎች ጨምሮ ከ10 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ በማታ ፕሮግራም 809 ተማሪዎችን፣ በቀን 3 ሺህ 39 እንዲሁም በርቀት 18 ተማሪዎቹን ለምርቃት አብቅቷል።
ከእነዚህ መሀከል 5045 በመጀመሪያ ዲግሪ ፣ 313 በ3ኛ ዲግሪ እና 2226 በማታ ፕሮግራም ያሰለጠናቸው መሆናቸው ተጠቁሟል።
እንዲሁም በርቀት 180፣ በክረምት 2252፣ በስፔሻሊቲ 265፣ ከፍተኛ ዲፕሎማ በመምህርነት ፕሮግራም 269 ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው በአመቱ በአጠቃላይ 10561 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
በአመቱ የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 7350 ወንዶችን እና 3211 ሴቶች ተማሪዎቹን ለምረቃ አብቅቷል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.