Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ ምክክሩ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንደሚያግዝ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ ምክክሩ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንደሚያግዝ የምክክር ኮሚሽኑ ገለጸ፡፡

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀረሪ ክልል ከመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሥራ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል፡፡

በመድረኩን ንግግር ያደረጉት የUረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ÷ ምክክሩ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለማስፈን ያግዛል ብለዋል።

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ወሳኝ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት እንዲቻል ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የተቋቋመ ስለመሆኑ የምክክር ኮሚሸኑ ኮሚሽነሮች አስረድተዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሸነር አምባሳደር መሐመድ ድሪል በበኩላቸው እንዳሉት÷ ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ወዲህ ለምክክሩ የሚያግዙ ስራዎች አከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ የሚስተዋሉ አለመግባባቶችንና ችግሮችን ለመፍታት ምክክር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ደግሞ ኮሚሸነር መላኩ ወ/ማርያም ናቸዉ።

ከምክክሩ በኋላ በሀገሪቱ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት፣ ወቅታዊ ችግሮችን በሠላማዊ መንገድ ለመፍታትና ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ከማስቻል በተጨማሪ፥ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት ለመገንባት እንደሚያግዝ አመላክተዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የUረሪ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች÷ የኮሚሽኑ ራዕይ ለሀገር ሠላምና አንድነት ወሳኝ ሚና እንዳለው ጠቅሰው÷ ለምክክር ኮሚሽኑ ስራ ስኬታማነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በተሾመ ኃይሉ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.