Fana: At a Speed of Life!

አጥፊ የሆኑ የጉግል ክሮም እና የማይክሮሶፍት ኤጀ ቅጥያዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎችን ለመረጃ ጥቃት እንዳጋለጣቸዉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አጥፊ የሆኑ የጉግል ክሮም እና ማይክሮሶፍት ኤጀ የመረጃ ማፈላለጊያ ቅጥያዎች  በሚሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎችን ለመረጃ ስርቆትና  ጥቃት ተጋላጭ እንዳደረጋቸዉ አቫስት ኩባንያ ገለጸ፡፡

የአቫስት ኩባንያ የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች በበርካታ የጉግል ክሮም እና የማይክሮሶፍት ኤጀ የመረጃ ማፈላለጊያ ቅጥያዎች ውስጥ የተደበቀ ተንኮል አዘል ሶፍትዌር ማግኘታቸዉን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ሶስት ሚሊየን የጉግል ክሮም እና የማይክሮሶፍት ኤጅ ተጠቃሚዎች ለመረጃ ስርቆት እና የመረጃ ማጥመድ ጥቃት መጋለጣቸዉን ተመራማሪዎቹ አሳዉቀዋል፡፡

ቅጥያዎቹ ተጠቃሚዎች ከፌስቡክ፣ ከቪሜዎን /Vimeo/ ፣ ከኢንስታግራም እና ከዩቲዩብ ከመሳሰሉ ታዋቂ ከሆኑ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ቪዲዮዎችን ለማዉረድ እንዲያግዙ ታስበው የተሰሩ መሆናቸዉም ታዉቋል፡፡

በእነዚህ አጥፊ ቅጥያዎች ሳቢያ የተጠቃሚዎች የትውልድ ቀን፣ የኢ-ሜይል አድራሻዎችን እና የሚጠቀሙበትን ስልክ ሆነ ኮምፒዉተር ስም ለጥቃት የተጋለጠ ይሆናል፡፡

ከዚህ ባለፈም ተጠቃሚው ኮምፒዉተር ወይም ስልኩን ከፍቶ የገባበት እና የወጣበት ጊዜ መረጃ፣ የኦፕሬቲንግ ሲስተም መረጃ፣ ሲጠቀምባቸዉ የነበሩ የመረጃ ማፈላለጊያዎችን ስም ጨምሮ የአይፒ አድራሻዎችን መረጃ ይሰበስባሉ  ተብሏል፡፡

እነዚህ አጥፊ ቅጥያዎች በብሮዉዘሮች ላይ አሁንም ድረስ እንደሚገኙ የገለጸዉ አቫስት ተጠቃሚዎች ቅጥያዎችን እንዳይተገበሩበማድረግ አገልግሎቱን ማቋረጥ እንዳለባቸዉ መምከሩንከኢመድኤ ያገኘነው ዘገባ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.