Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የደቡብ  ክልል ምክትል ርእሰ መስተደድር  አቶ እርስቱ ይርዳ በጋሞ ዞን የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የህዝብ  ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የደቡብ  ክልል ምክትል ርእሰ መስተደድር  አቶ እርስቱ ይርዳ በጋሞ ዞን በቦንኬ ወረዳ  የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን መርቀው ከፈቱ፡፡

መሠረተ ልማቶቹ የመንግስት  መስሪያ ቤቶች  እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሲሆኑ ÷ ከ22 ሚልየን ብር በላይ ወጪ የተረገባቸው ና አብዛኛው ወጪም በህብረተሰቡ ነው የተሸፈነ መሆኑ ተመላክቷል።

የአካባቢው ነዋሪዎችና የግንባታው አስተባባሪዎች በሰጡት አስተያየት ለሁሉም  ነገር መንግስትን  መጠበቅ የህብረተሰቡን ችግር ፈቅ እንደማያደርገው  በማንሳት÷ ሁሉም በትብብር  ከተነሳና ከሰራ  የሀገሪቱን  ብልፅግና ማረጋገጥ ይቻላል ነው ያሉት።

የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ  አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በዚህ ወቅት ባደረጉት  ንግግር÷  የቦንኬ ወረዳ ነዋሪዎች የፈፀሙት ተግባር ትብብር ካለ ሁሉ ነገር እንደሚቻል ማሳያ ነው በማለት ለሁሉም ትምህርት  የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የደቡብ  ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ  አቶ ጥላሁን ከበደ  በበኩላቸው ÷ ከቦንኬ ወረዳ ጋር እኩል የወረዳነት መዋቅር ካገኙ አካባቢዎች በርካቶች እዚህ ግባ የሚባል የልማት ስራ   እንዳላከናወኑ በመጥቀስ የቦንኬ ነዋሪዎች   ይሄን መሰል ጀግንነት  መፈፀማቸው የሚያኮራ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም መንግስትና ህብረተሰቡ በመተባበር በርካታ መሰረተ ልማቶችን ለማስመረቅም ይበቃሉ  ነው ያሉት።

የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የደቡብ  ክልል  ምክትል ርእሰ መስተደድር  አቶ እርስቱ ይርዳ  ለተደረገላቸው አቀባበል  ምስጋና በማቅረብ  ባዩት ሁሉ መደነቃቸውን  ተናግረዋል።

የቦንኬ ወረዳ ነዋሪዎች  መንግስትን ሳይጠብቁ ላደረጉት  ልማታዊ ተሳትፎ ከፍ ያለ ምስጋና ያቀረቡት አቶ እርስቱ ሌሎች ዞኖችና ወረዳዎች ከዚህ ህዝብ መጥተው ትምህርት  ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።

ለተገነቡ መሰረተ ልማቶቾና የመንግስት  መስሪያ ቤቶች የውስጥ ቁሳቁሶችን  ድጋፍ ለማድረግና የተጀመሩ የመንገድ ግንባታዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ  የክልሉ  መንግስት ይሰራል በማለትም ቃል ገብተዋል።

የህዝብ  ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ  በበኩላቸው ÷ የቦንኬ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ ትክክለኛ ስለመሆኑ በልማት በመረጋገጡ  ለነዋሪዎቹ ምስጋና አቅርበዋል።

አከባቢው ለደጋ ፍራፍሬ እና ለእንስሳት  እርባታ ምቹ በመሆኑ ህብረተሰቡ በዚህ ዘርፍ በስፋት በመሳተፍ የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብም  መልእክት አስተላልፈዋል ።

በአንድነትና በጋራ ሁሉም ለሀገርና ለህብረተሰቡ  ለውጥ እንዲሰራም ዋና አፈ ጉባኤው  ጥሪ ማቅረባቸውን ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.