Fana: At a Speed of Life!

ኡጋንዳና ታንዛኒያ የ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኡጋንዳና ታንዛኒያ፤ የነዳጅ አምራቾቹ ቶታልና ሲኤንኦኦሲ የ3 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት ስምምነት ላይ ደረሱ፡፡

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሩ ከምዕራባዊ ኡጋንዳ ወደ ዓለም አቀፉ ገበያ ድፍድፍ ነዳጅ ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡

የድፍድፍ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመሩ 1 ሺህ 445 ኪሎሜትር ይሸፍናል፡፡

ባለፈው ዓመት የብሪታንያው ነዳጅ አምራች ቱሎዎ ከሀገሪቱ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፈረንሳዩ ቶታልና የቻይናው ሲኤንኦኦሲ የነዳጅ ማውጫውን ባለቤትነት መያዛቸው ተነግሯል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የታንዛኒያዋ አዲሷ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሐሰን የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን ወደ ኡጋንዳ  አድርገዋል፡፡

ፕሬዚዳንቷ ከኡጋንዳ አቻቸው ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በመሆን በስምምነቱ ወቅት መታደማቸው ተገልጿል፡፡

የባህር በር የሌላት ኡጋንዳ በፈረንጆቹ 2006 ስድስት ቢሊየን በርሜል የሚገመት ነዳጅ እንዳገኘች ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.