Fana: At a Speed of Life!

ኢራን፣ ሩሲያ እና ቻይና የጋራ የባህር ኃይል ልምምድ ሊጀምሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢራን፣ የሩስያ እና የቻይና ባህር ሃይሎች በህንድ ውቅያኖስ ላይ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ነገ ሊጀምሩ ነው፡፡
“ማሬን ሴኩሪቲ ቤልት 2022” የተሰኘው የሀገራቱ የባህር ሃይል ልምምድ ዓላማ የአለም አቀፍ የባህር ንግድ ደህንነትን ለማጠናከር፣ ንግድን ለማስፋፋት፣ የባህር ላይ ሽብርተኝነትን እና የባህር ላይ ወንበዴዎችን ለመዋጋት እንዲሁም በታክቲካል ስራዎች ላይ ልምድ ለመለዋወጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ልምምዱ በህንድ ውቅያኖስ ሰሜናዊ ክፍል በ17ሺህ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ እንደሚካሄድ ዘገባው አስታውሷል።
የመጀመሪያው “ማሬን ሴኩሪቲ ቤልት 2019” ከተካሄደ በኋላ ይህ ሦስተኛው ወታደራዊ ልምምድ መሆኑን አናዶሉ ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.