Fana: At a Speed of Life!

ኢራን በኒውክሌር ዙሪያ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውይይት እንደማታደርግ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢራን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኒውክሌር ዙሪያ ሀገራቸው ከአሜሪካና ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውይይት እንደማታደርግ አስታውቋል፡፡

ቴህራን ከአሜሪካና ከሦስቱ የአውሮፓ ሀገራት ጋር ኢ-መደበኛ ውይይት የማካሄድበት ወቅት አይደለም ብላለች፡፡

ይህ የተሰማው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በኒውክሌር ዙሪያ የሚደረግን ኢመደበኛ ውይይት አስመልክቶ ያቀረቡትን ሃሳብ ተከትሎ ነው፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ በኒውክሌር ስምምነት ዙሪያ ዳግም ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር፡፡

ሆኖም ኢራን በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ በኩል በስምምነቱ ዙሪያ ውይይቱ እንዲቀጥል ከሁሉም በፊት አሜሪካ በተናጠል የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳት እንዳለባት አሳስባለች፡

አሜሪካ በበኩሏ ኢራን ጥሰት እየፈጸመችበት የምትገኘውን የ2015ቱን ስምምነት ልታከብር ይገባታል ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡

በተጨማሪም አሜሪካ በኢራን ውሳኔ ማዘኗን ገልጻ ሁለቱንም ወገን የሚጠቅም ትርጉም ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለመመስረት እንደምትሰራ ገልጻለች፡፡

የኢራን የኒውክሌር ስምምነት በ2015 የተደረሰ ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በተናጠል ከስምምነቱ መውጣቱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.