Fana: At a Speed of Life!

ኢራን ወደ ሃገሯ ለሚገቡ አውሮፓውያን ከባድ የኮቪድ-19 እገዳዎችን ጣለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢራን ወደ ሃገሯ ለሚገቡ አውሮፓውያን ከባድ የኮቪድ-19 እገዳዎችን መጣሏን አስታወቀች፡፡

ከአውሮፓ ወደ ኢራን የሚመጡ ተጓዦች የኮሮና ምርመራ ካደረጉ በኋላ ለሁለት ሳምንታት ያህል ራሳቸውን እንዲያገሉ ይገደዳሉ ሲሉ የብሔራዊ የኮሮና ቫይረስ ግብረ ኃይል ባለሥልጣን ተናግረዋል ፡፡

የግብረ ሃሉ ቃል አቀባይ አሊሬዛ ራይሲ እንደተናገሩት ከአውሮፓ የሚመጡ ሰዎች የኮቪድ-19 የምርመራ ውጤታቸው ቫረሱ እንደሌለባቸው ቢያመላክትም እንደገና መመርመር ግድ እንደሚሆንና ራሳቸውን አግልለው ለሁለት ሳምንታት እንደሚቆዩ ገልጸዋል፡፡

ይህ ህግ ከመውጣቱ በፊት ከአውሮፓ የሚመጡ ተጓዦች ከኮቪድ-19 ነጻ መሆናቸውን የሚያመላክት መረጃ ብቻ ይጠበቅባቸው እንደነበር መረጃው ያሳያል፡፡

ከኢራን አጎራባች አገራት እና ከሌሎች አገራት የሚመጡ ተጓዦች ወደአገሪቱ ከመግባታቸው በፊት ምርመራ አድርገው ነጻ መሆን እንዳለባቸው ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም አዲሱ ህግ የሚተገበርበት ቀን ግልጽ አለመደረጉም ነው የታወቀው፡፡

የኢራን ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ ቫይረሱ እንዳይስፋፋ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ ይህ ካልሆነ በአገሪቱ በሁለት ወራት ቫይረሱ ሊያገረሽ ይችላል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአገራቸው የሚመረተው የኮቪድ-19 ክትባት በመጋቢት ወር ይጠናቀቃል ተብሎ እንሚጠበቅ ጠቅሰው፤ ይህን ክትባት በቅርቡ ለዜጎች መሰጠት እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡

በኢራን እስካሁን ከ 1ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 57 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.