Fana: At a Speed of Life!

ኢራን የቪዬናው የኒውክሌር ውይይቱ ፍላጎቶቿን ያላሟላ መሆኑን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢራን የኒውክሌር ውይይቱ አወንታዊ ቢሆንም የእሷን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ያሟላ አለመሆኑን ገለጸች።

በተያዘው የፈረንጆቹ ነሐሴ ወር መጀመሪያ በኦስትሪያ ቪዬና የ2015ቱን የኒውክሌር ስምምነት ዳግም ወደ ነበረበት ለመመለስ ያለመ ውይይት ተካሂዷል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተደረገው ውይይት አዎንታዊ ቢሆንም የቴህራንን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ አላሟላም ብሏል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በአውሮፓ ህብረት አሸማጋይነት የተካሄደው ውይይት ጥሩ መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል።

ነገር ግን በውይይቱ የታየው መሻሻል የኢራንን ህጋዊ ጥያቄዎች ያላከተተ መሆኑን አንስተዋል።

ሌሎች ወገኖች በተለይም አሜሪካ የኢራንን “ቀይ መስመር” ግምት ውስጥ በማስገባት፥ ቴህራን በአጠቃላይ የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር ቃል የተገባላትን ጥቅም የምስታገኝ ከሆነ “በቅርብ ጊዜ ውስጥ” ስምምነት ላይ መድረስ እንደሚቻል ገልጸዋል።

በፈረንጆቹ ነሐሴ 8 ከተጠናቀቀው የመጨረሻው ውይይት በኋላ የአውሮፓ ህብረት ሁሉም ወገኖች ስምምነት ላይ ለመድረስ አስፈላጊውን የፖለቲካ ውሳኔ እንዲወስኑ አሳስቧል።

አሜሪካ በህብረቱ ሃሳብ ስትስማ በአንጻሩ ኢራን ያልተመለሱ ሌሎች ጉዳዮች አሉ በማለት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥባለች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የአውሮፓ ሕብረት የመጨረሻ በሚል ባወጣው ፅሁፍ ላይ፥ ቴህራን ያላትን አስተያየት በመጨረሻው ቀን እንደምታሳውቅ መግለጹን አልጀዚራ በዘገባው አመላክቷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.