Fana: At a Speed of Life!

ኢሰመጉ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ ቦታዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን የሕይወትና አካላዊ ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆን አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ /ኢሰመጉ/ በትግራይ ክልልና አዋሳኝ ቦታዎች ያለው እንቅስቃሴ የሰላማዊ ሕዝብን የሕይወትና አካላዊ ደህንነት ብሎም የሲቪል ንብረቶችን ደህንነት አደጋ ላይ የማይጥል እንዲሆን እና ሁሉም ወገኖች ግጭት አባባሽ ከሆኑ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረበ፡፡
 
ኢሰመጉ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና መላው ኢትዮጵያውያን ግጭቱ ተባብሶ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት በመንቀሳቀስ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ በሁሉም ወገኖች ላይ ግፊት እና ጫና እንዲያደርጉ ኢሰመጉ ጠይቋል፡፡
 
መንግሥትም በየጊዜው በሚፈጠሩ ነገሮች ዙሪያ ተከታታይ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ኢሰመጉ አሳስቧል፡፡
 
ሁሉም የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና ብዙኃን መገናኛ ድርጅቶች ሕዝብን ለግጭት የሚያነሳሱ እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የሚዳርጉ የሐሰት ዜናዎችን፣ የተሳሳቱ፣ የተዛቡ እና የተበከሉ መረጃዎችን ከመናገር እና ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.