Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሱዳን ያጋጠማቸውን ችግር በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም አላቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሱዳን ያጋጠሟቸውን ችግሮች በወንድማማችነትና በመልካም ጉርብትና መንፈስ የመፍታት አቅም አላቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የሱዳንና የኢትዮጵያ ህዝቦች ወንድማማቾች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ችግር መኖሩ ግልፅ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ነገር ግን ሁለቱ ሀገራት እነዚያን ችግሮች ለመፍታት ሊጥሩ እና ሊተባበሩ ነው የሚገባው ብለዋል።

የሀገራቱን መጋጨት የሚፈልጉ መንግስታት ወይም ሌሎች ወገኖች ቢኖሩም እነዚህ አካላት ከሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ግጭት የሚያተርፉት አይኖርም ሲሉ አስረድተዋል።

በውጭ ሀይል ግፊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ውዝግብ ሊኖር እንደማይገባ በማንሳትም ራሳችንን ልንቆጣጠር እና ከግጭት ልንቆጠብ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

በመካከላችን የጠላትነት መንፈስ ሊኖር አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ይልቁንም በልማት ልንተባበር እና አብረን ልናድግ ይገባናል ነው ያሉት።

“ሱዳንና ኢትዮጵያ ዘላቂነት ባለው የወንድማማችነትና የመልካም ጉርብትና መንፈስ ያጋጠሟቸውን ችግሮች ሁሉ የመፍታት አቅም እንዳላቸው እናምናለን” ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.