Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና አልጄሪያ በተለያዩ መስኮች በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 21 ፡ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና አልጄሪያ በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጀሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ሚኒስትሮቹ ሁለቱ ሃገራት በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

ሃገራቱ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ ያላቸውን ሚና በሚያጠናክሩበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ከዚህ ባለፈም በህዳሴ ግድና በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ ዙሪያም ምክክር አድርገዋል፡፡

በተያያዘም ሚኒስትሩ ከፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የአልጄሪያውን ፕሬዚዳንት አብዱል መጂድ ቲቦንን መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ አስረክበዋል።

ውይይታቸው በዋናነት በሃገራቱ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ የአፍሪካ ሰላምና ደህንነት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

የአልጀሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራምታኔ ላማምራ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.