Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ካዛኪስታን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ካዛኪስታን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ አብረው ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት መደረጉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ከካዛኪስታን አምባሳደር ባርሊባይ ሳንዲኮቭ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ ባለሀብትን በመሳብ እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።

በኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዘርፍ እየተከናወነ ስለሚገኘው ተግባር፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ማበረታቻዎችን በተመለከተ አቶ ሳንዶካን

ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፥ አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮችም ሆነ የልምድ ልውውጥ በማድረጉ ረገድ አጋርነታቸውን ገልፀዋል።

አምባሳደር ባርሊባይ ሳንዲኮቭ በበኩላቸው፥ ሀገራቸው ወደብ አልባ መሆኗ ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚያመሳስላት ጠቅሰዋል፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዴት ምርታቸውን ወደ ውጭ እንደሚልኩ፣ የባቡር ማጓጓዣዎችን ግንባታ በተመለከተ እንዲሁም ከሀገራቸው ባለሃብቶች ጋር እንዴት የንግድ ትስስር ማድረግ እንደሚቻል በማንሳት ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ ቦሌ ለሚ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የጎበኙ ሲሆን ከፓርክ ስራ አስኪያጆችና ባለሃብቶች ጋር መወያየታቸውንም ከኮርፖሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.