Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የኮሪያው ኤግዚም ባንክ የ93 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ ጋር የ93 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረመች።

ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና የኮሪያው ኤክዚም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሺን ዲኦግ ዮንግ ተፈራርመውታል።

የብድር ስምምነቱ በሁለት ምዕራፎች ለሚተገበሩት የአዲስ አበባ የፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ግንባታ እና ለመሬት መረጃ አስተዳደር ስርአት ማስፈጸሚያ ይውላል ተብሏል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግ፣ በትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋ ምክንያት የሚደርሰውን የሃብት ብክነት መቀነስና በዘርፉ ምቹ ሁኔታን መፍጠር አላማው ያደረገ ነው ተብሏል።

63 ሚሊየን ዶላሩ ለዚህ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ሲሆን፥ በአምስት አመታት ውስጥ የሚተገበር ነው።

ለሁለተኛው ምዕራፍ ማስፈጸሚያ ደግሞ 30 ሚሊየን ዶላሩ የተመደበ ሲሆን፥ በስድስት አመታት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል ነው የተባለው።

ይህ ፕሮጀክት ትክክለኛ የመሬት መረጃ አስተዳደርን በማስፈን የሚፈጠሩ ግጭቶች መቅረፍ፣ የግብር አሰባሰብ ስርአቱን ማዘመን የሚያስችል ስርአት መዘርጋት እና የመሬት አስተዳደር ስርአቱን ማዘመንን አላማው ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.