Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ተወያዩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ዋነኛ ተልዕኮዎች ከሆኑት ለኢትዮጵያ ወዳጅ የማብዛት፣ ገፅታ የመገንባት፣የውጭ ኢንቨስትመንት የመሳብ፣ ለኢትዮጵያ ምርቶች ገበያ የመፈለግና የዜጎችን መብት ከማስከበር በተጨማሪ ጠቃሚ ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር እንዲገባ ማመቻቸት ነው ሲሉ አስፍረዋል፡፡

በመሆኑም የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት የሚወክሉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ያደረገው ውይይት ጠቃሚ መሆኑን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶር አብርሃም በላይ ሃብት በማፈላለግ፣ በዘርፉ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብና ተያያዥነት ባላቸው ዘርፎች ዲፕሎማቶች የሀገሪቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ እንዲያግዙ ጠይቀዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ እምየ ቢተው በበኩላቸው ኢትዮጵያ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያጸደቀቻቸውን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ለዓለም ማሳወቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዘርፉ ሥራ በመፍጠር፣ ገቢ በማመንጨትና የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ያለውን ፋይዳ በመረዳት አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶችን ወደ አገር ማምጣት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.