Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በተመለከተ ሱዳን ትሪቢዩን ሀሰተኛ ዜና አሰራጭቷል- ኤምባሲው

አዲስ አአበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ትሪቢዩን ኢትዮጵያን በተመለከተ ያሰራጨው ያልተረጋገጠ ዜና እንዳሳዘነው በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

ሱዳን ትሪቢዩን ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን የሚገቡ ሰዎችን ለመከላከል ኢትዮጵያ ሰራዊቷን ወደ ድንበር አያስጠጋች ነው የሚል ዘገባ ማውጣቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ሲያካሂድ የነበረውን ህግን የማስከበር ዘመቻ አጠናቆ መንግስት ወንጀለኞችን እና የህወሃት አመራሮችን በቁጥጥር ስራ ለማዋል እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ኤምባሲው አስታውቋል።

መንግስት ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስራ የማዋል ስራ ከመስራቱ ባሻገር በህወሃት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን እንደገና የመገንባት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ነው የገለፀው።

በተጨማሪም ህግን በማስከበር እርምጀው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ እንደሚገኝና ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየሰራ እንደሚገኝ ኤምባሲው ጠቁሟል።

ነገር ግን ሱዳን ትሪቢዩን ማንነታቸው የማይታወቅ የአይን ምስክሮችን በመጥቀስ በአካባቢው ያለውን ጦርነት  ሸሽተው ስደተኞች ወደ ሱዳን እየገቡ መሆኑን እና ኢትዮጵያም ስደተኞቹን ለማስቆም ወታደሮቿን ወደ ሱዳን ድንበር አስጠግታለች ሲል ሀሰተኛ ዘገባ አውጥቷል ብሏል ኤምባሲው።

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያውን በተመለከተ ካስቀመጠው አሃዝ በማጋናን የስደተኞችን ቁጥር በዘገባው ላይ ማስፈሩ ተጠቁሟል።

የጋዜጠኝነት መርህ በሚቃረን መልኩ የኢትዮጵያ መንግስት ሀሳብ ሳያካትት ወገንተኛ የመረጃ ምንጭ ብቻ በመጠቀም ዜናውን እንዳሰራጨም አንስቷል።

በመሆም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም የሚያጠለሽ እና ዋጋ የሚያሳጣ ዘገባውን ሱዳን ትሪቢዩን እንዲያስተካል አሳስቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.