Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊ እርቅ ምንድን ነው? በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ኢትዮጵያዊ እርቅ ምንድን ነው? በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ፡፡
የመድረኩ ዓላማ የሰላም ሚኒስቴር ባለፉት ሶስት ወራት በየደረጃው ሲያካሄድ ለነበረው የማህበረሰብ አቀፍ የምክክር መድረክ የማጠቃለያ ዝግጅት አዲስ ሃሳብ እና ግብአት እንዲሆን ለማስቻል ነው ተብሏል።
በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ እርቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
እርቅ አዲስ እድል፣ አዲስ ዘመን እና አዲስ አስተሳሰብ የሚገኝበት መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዲኤታዋ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች ተቀባይነት ያለው ይህን እሴት ለሀገራዊ ጉዳይ መጠቀም እና ችግሮችን መፍታት ይቻላል ብለዋል።
በመድረኩ የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ አደረጃጀቶች የመጡ ወጣቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊዎች ናቸው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.