Fana: At a Speed of Life!

በፖላንድ የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፖላንድ ጊዲኒያ የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንዶችም በሴቶችም 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
በወንዶች በተካሄደው የዓለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮና ኢትዮጵያው አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 59 ደቂቃ 08 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ደረጃ ይዞ ውድድሩን ማጠናቀቅ ችሏል።
ውድድሩን ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በ58 ደቂቃ 49 ሴኮንድ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኬኒያዊው ካንዴ ደግሞ 58 ደቂቃ 54 ሴኮንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሷል።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 3ኛ በመውጣት ውድድሩን ስታጠናቅቅ፤ ዘይነባ ይመርና አባባል የሻነህ 4ኛ እና 5ኛ፣ ነጻነት ጉደታ 8ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
በውድድሩ ኢትዮጵያ በአምስት አትሌቶች ያለምዘርፍ የኋላው ደንሳ፣ ነፃነት ጉደታ ከበደ፣ ዘይነባ ይመር ወርቁ፣ አባበል የሻነህ ብርሃኔ እና መሰረት ጎላ ሲሳይ ተወክላለች።
የዓለም አትሌቲክስ በውድድሩ በግልም ሆነ በቡድን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች ሽልማት እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል።
በግል ከአንደኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች በተከታታይ የ30 ሺህ፤ የ15 ሺህ እና የ10 ሺህ የሜሪካ ዶላር ሽልማት ያገኛሉ።
በቡድን ከአንደኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶች የ15 ሺህ፤ የ12 ሺህ እና የ9 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በተከታታይ ሽልማት ይሰጣቸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.