Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለተመድ ሀሳቦች ተግባራዊነት ቁርጠኛ ሆና ትቀጥላለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ በቪድዮ ኮንፈረንስ በተካሄደ ስብሰባ ላይ መልእክት አስተላልፈዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች ሀገር መሆነኗን አንስተዋል።
 
በዚህምኢትዮጵያ በድርጅቱ ቻርተር ላይ የተቀመቱትን ደንቦች የጋራ ደህንነት እና የብዙሃነት መርሆዎችን ተግባራዊነት ቁርጠኛ ሆና እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።
 
በዚህ ወቅት የሰው ልጅ የሚያጋጥማቸውን ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቁ ተግዳሮቶችን እና ስጋቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረትም የበኩሏን ለመወጣት ቁርጠኛ ናትም ነው ያሉት።
 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ለድርጅቱ የሰላም ማስከበር ተልእኮዎች በሰራቻቸው ስራዎች ሁሉ ኩራት ይሰማናል ብለዋል።
 
ከዚያም ባለፈ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የለውጥ አጀንዳ ለሆነው የዘላቂ የልማት ግቦች መሳካት የበኩሏን ሚና ለመጫወት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
 
ድርጅቱ ከ75 ዓመታት በፊት የድርጅቱ መስራቾች ዓላማ አድርገው የተነሱት ተተኪውን ትውልድ ከጦርነት መርገም የማዳንና የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ የማድረግ ታላቅ ራዕይን ሰንቀው እንደነበርም አስታውሰዋል።
 
በእንደዚህ ዓይነት ታላቅ ራዕይ ድርጅቱ ሌላ አሳዛኝ የዓለም ጦርነት እንዳይከሰት ከመከላከል ባለፈ ለሰው ልጆች በጣም አስፈላጊ ድጋፍን በመስጠት ላይ ነው ብለዋል።
 
በዚህም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ሆነው ሰላምን ለማስፈን እና ለማረጋገጥ ፣ግጭቶችን በመፍታት እና በህይወት አድን ስራ ለተሰማሩ ሰራተኞች ሁሉ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አያይዘውም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ በጤና ስርዓቱ ላይ ተግዳሮት በመሆን የአለም ኢኮኖሚን ጎድቶታል ሲሉ ተናገረዋል።
 
በዚህም ምክንያት በዘላቂ ልማት ግቦች በኩል ሊመዘገቡ የሚገባቸው ለውጦች በወቅቱ እንዳይመጣ ማድረጉን አንስተዋል።
 
ስለሆነም ድርጅቱ በእነዚህ ዓመታት በውስጡ አዲስ እና ታይቶ የማይታወቁ ተግዳሮቶች ሲገጥሙት እንደነበር ተግዳሮቶችን በመቋቋም እዚህ መድረሱን አስታውሰው÷ አሁንም ዓላማውን ለማሳካት ከአዲሶቹ ዓለምአቀፍ እውነታዎች ጋር መላመድ ይኖርበታልም ነው ያሉት።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.