Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቀልጣፋ እና ዘላቂ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖራት በቁርጠኝነት ትሠራለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ÷ የሎጀስቲክስ እና የጊዜን ወጪ በመቀነስ፣ ዘላቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ሀገሪቷ ያላትን ቁርጠኝነት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገለጹ።

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ÷ በቻይና ቤጂንግ እየተካሄደ ባለዉ ሁለተኛው የተመድ ዓለም አቀፍ ዘላቂ የትራንስፖርት ኮንፈረንስ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሯ በቤጂንግ በተጀመረው የበይነ-መረብ ኮንፈረንስ በተደረገ ዉይይት÷ በኢትዮጵያ የትራንስፖርት መሠረተ ልማትና አገልግሎትን በማስፋፋት የወጪና ገቢ ንግድን ለማቀላጠፍ ብሎም የሎጀስቲክስን ዉጤታማነት ለማሻሻሸል መንግስት ስለሰጠዉ ትኩረት አብራርተዋል።

በኢትዮጵያ ከቆዳ ስፋትና ከህብረተሰቡ ፍላጎት አንጻር የትራንስፖርት አገልግሎትና መሠረተ ልማት በሚፈለገዉ መጠን ባለመስፋፋቱ ለኢኮኖሚ ዕድገት እንቅፋት ሆኖ መቆየቱንም አንስተዋል።

በቅርቡ ተግባራዊ በተደረገዉ ብሔራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ የትራንስፖርት መሠረተ ልማትና አገልግሎትን ለማስፋፋት ትኩረት የተሰጠ መሆኑንና የሥራ ዕድሎችንም ለማስፋት በ10 ዓመቱ የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ የልማት ዕቅድ ላይ መቀመጡን እና ግቦቹንም ማብራራታቸው ታውቋል።

ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር በማድረግ የሎጂስትክስ ጊዜና ወጪን በመቀነስ ለዘላቂ ትራንስፖርት ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነትና ዝግጁነት መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የቻይና ሪፐብሊክ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሊ ዥያኦፕኝግ÷ በመድረኩ ንግግር እንዲያደርጉ ስለጋበዟቸዉ አመስግነዉ÷ የትራንስፖርት አገልግሎትና መሠረተ ልማት መስፋፋት ለአንድ ሀገር ዘላቂ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት እንደሆነና ለሁሉም ዘርፎች ስኬት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል – ሚኒስትሯ።

ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ መንግስት በሰጠዉ ትኩረት ትልቅ በጀት ተመድቦ እየተሠራ መሆኑንም ነው ያብራሩት።

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ማስተላፋቸዉ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.