Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በመድሀኒትና የህክምና ቁሳቁስ ምርት ላይ የሀገር ውስጥ ምርትን ለማበረታታት ሀሳብ አቀረበች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት 148ኛ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ስብሰባውን አካሄደ።

በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው ስብሰባ የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተሳትፈዋል።

ዶክተር ሊያ የጤና ተደራሽነትን እና የአቅርቦት ችግርን ለመፍታት በዘርፉ የሀገር ውስጥ ምርት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

በመድረኩም ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ የመድሀኒት እና የህክምና ቴክኖሎጂ ምርት ማበረታቻ ላይ ያዘጋጀችውን የመነሻ ሀሳብ አቅርበዋል።

በዚህም የአቅርቦት ችግርንና ተደራሽነትን ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል።

የዓለም የጤና ድርጅትም አመራር በመስጠት እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ አጋርነቱን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ጥራታቸውን በጠበቁ የሀገር ውስጥ የመድሀኒትና የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ምርቶች አገልግሎት መስጠት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባልም ነው
ያሉት።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.