Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና ሰባት ሜዳሊያዎችን አገኘች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ሲካሄድ በቆየው የምሥራቅ አፍሪካ የጠረጴዛ ቴኒስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሰባት ሜዳሊያዎችን በማግኘት አጠናቀቀች።

ከሚያዚያ 27 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዘጠኝ አገራት የተሳተፉበት ውድድር ለአራት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተካሂዷል።

በዚህ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ብሄራዊ ቡድን ሰባት ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል።

ከሰባቱ ሜዳሊያዎች ሁለት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ሦስት የነሐስ ሜዳሊያዎችን ነው ኢትዮጵያ ያገኘችው።

የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ በወንዶች የነጠላ ውድድር በአትሌት ደራራ መኮንን የተገኘ ሲሆን ፥ ሁለተኛው የወርቅ ሜዳሊያ ደግሞ በሴቶች የቡድን ጨዋታ የተገኘ ነው።

በውድድሩ በቡድን ሁለት ሀገራት፤ በነጠላ ደግሞ ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃ የወጡ ስፖርተኞች ምሥራቅ አፍሪካን ወክለው በ2022 ዓ.ም በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ውድድር ላይ የሚካፈሉ ይሆናል።

በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ በቡድን ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድር በሁለቱም ጾታ ተካፋይ መሆኗን አረጋግጣለች።

በነጠላ ጠረጴዛ ቴኒስ ውድድርም በሴቶች አምስት፤ በወንዶች ደግሞ አራት ስፖርተኞች መሳተፍ እንደሚችሉ መረጋገጡን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.