Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሴቶች የ3ሺህ ሜትር መሠናክል ውድድር ብርና ነሐስ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሎምቢያ እየተካሄደ በሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች የ3ሺህ ሜትር የመሠናክል ውድድር ኢትዮጵያ ብር እና ነሐስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች፡፡
ሌሊት ላይ በተካሄደ የፍጻሜ ውድድር÷ አትሌት ሲንቦ ዓለማየሁ 9 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ለሀገሯ አስገኝታለች፡፡
እንዲሁም አትሌት መሠረት የሻነህ 9 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ ከ2ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሦስተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የነሐስ ሜዳሊያ ማስገኘቷን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ኬንያ በርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዳለች።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.