Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በበጀት አመቱ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከኢንቨስትመንት ዘርፍ ለማግኘት እየሰራች ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በበጀት አመቱ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከኢንቨስትመንት ዘርፍ ለማግኘት እየሰራች መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በኢንቨስትመንት ህጉ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን አስመልክቶ ለአሜሪካና ለካናዳ ባለሃብቶች ገለጻ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ካካሄደችው የኢኮኖሚ ሪፎርሞች መካከል አንዱ የኢንሸስትመንት ህጉን ማሻሻል ነው።

ከዚህ በፊት በዘርፉ የነበረው የህግ ማዕቀፍ የውጭ ባለሃብቶች በስፋት እንዳይሳተፉ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን በተደረገው ሪፎርም በርካታ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን አብራርተዋል።

በበጀት አመቱም 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ከዘርፉ ገቢ ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባስከተለው ቀውስ በዘርፉ እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በመቋቋም እቅዱን ለማሳካት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በኢንቨስትመንት ህጉ ላይ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት የሆኑ ስራዎች ውስን እንደነበሩ አስታውሰው፤ መንግስት እየተከተለ ያለው አቅጣጫ ይህን የሚለውጥ መሆኑን አስረድተዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የንግዱ ማህበረሰብ አባላት በበኩላቸው የተደረጉት ማሻሻያዎች ሃገሪቷ ለባለሃብቶች ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ኤርሚያስ እሸቱ “ከዚህ በፊት የነበሩት ህጎች ለውጭ ባለሃብቶች አስቻይ ሁኔታዎች ያልፈጠሩ ነበሩ” ብለዋል።

የአሜሪካው ቫርዳንት ኮንሰልቲንግ ማናጀር ወይዘሮ ትዕግስት ገረመው በበኩላቸው በመንግስት በኩል እየተደረጉ ያሉት ማሻሻያዎች መልካም የሚባሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

ሆኖም ከመሬት አስተዳደር፣ ከግብር እና ከውጭ ምንዛሬ ጋር የነበሩትን ችግሮች ለመፍታት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አሁንም ወሳኝ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

መንግስት የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ የፈጠራቸውን ምቹ ሁኔታዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር መስራት አለበት” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.