Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተመድ የሰላም ማስከበር የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ማስከበር የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በደቡብ ኮሪያ ሴኡል እየተካሄደ ባለው በዚህ ስብሰባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በቪዲዮ የተቀረጸ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ለአፍሪካ ሰላም የሚከፍሉት መስዋዕትነት ለኢትዮጵያ ሰላም የሚከፈል መስዋዕትነት ነው ብለዋል።

ከሰላም ማስከበር ተልዕኮ ጋር በተያያዘ ባስተላለፉት መልዕክትም አባል አገራቱ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በተለይም በአፍሪካ አገራት ወታደር ማስፈራቸውን እንዲያቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የማጠናከር ፍላጎት እንዳላትም ሚኒስትር ዲኤታው አጽንኦት ሰጥተዋል።

አያይዘውም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሰላም ማስከበር ተልዕኮው አስፈላጊውን የገንዘብ እና ፖለቲካዊ ድጋፍ እንዲያደርግም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ስብሰባ በሰላም ማስከበር ተልዕኮው የህክምና እና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

በስብሰባው ላይ ከ100 በላይ አባል አገራት እና ድርጅቶች የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን ለማሻሻል በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.