Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በቱርክ-አፍሪካ ንግድ ፎረም በልዩ የክብር እንግድነት ልትሳተፍ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስከረም በሚካሄደው የቱርክ አፍሪካ ንግድ ፎረም ኢትዮጵያ በልዩ የክብር እንግድነት እንደምትሳተፍ የቱርክ ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ትብብር ፎረም አስታውቋል፡፡
የፎረሙ ፕሬዚዳንት ኡታኩ ብኒጊሱ በሰጡት መግለጫ÷ ፎረሙ በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ መስከረም 14 እና 15 ቀን 2022 ይካሄዳል ብለዋል፡፡
በፎረሙ÷ ከ1 ሺህ 250 በላይ በንግድ እና ቢዝነስ የተሰማሩ አፍሪካውያን ይሳተፋሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያም በዘንድሮው ዓመት በሚካሄደው ፎረም ላይ እንደምትሳተፍ ገልጸው÷ በፎረሙ ለሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን የንግድና ቢዝነስ ሰዎች ልዩ የአገልግሎት ቅናሽ ይደረግላቸዋል ብለዋል፡፡
የቱርክና አፍሪካ ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው÷ ዓለም ዓቀፍ የትብብር ፎረሙም ይህን ወዳጅነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ የበኩሉን አስተዋጽዖ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.