Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ ሽልማት እጩ ሆነች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2019 የአረንጓዴ ልማት አሻራ በሚል በተከለችው 4 ቢሊየን የዛፍ ችግኞች ለብሔራዊ የአየር ንብረት ለውጥ ሽልማት እጩ ሆና ተመረጠች።

ሽልማቱ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና የሚሰጥበት መሆኑን በብሪታኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በእጩ ዝርዝሩ ኢትዮጵያ ሌሎችን በማነቃቃት በሚል ምድብ ውስጥ መመደቧም ነው የተገለጸው።

በዚህም ኢትዮጵያ ከሴራሊዮኑ ንጎሊያጎርቡ የኮኮዋ ገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበር እና ከናይጄሪያው ጆስ ግሪን ሴንተር ጋር ዕጩ ሆና ቀርባለች።

ሽልማቱ አረንጓዴ ልማት ላይ የሚሰሩ ግለሰቦችን ጨምሮ፥ ድርጅቶች፣ ትምህርት ቤቶችና የፓርላማ አባላትን  ያጠቃልላል ተብሏል።

አሸናፊዎች በገለልተኛ ዳኞች የሚመረጡ ሲሆን፥ ለንደን ውስጥ በሚካሄድ ስነ ስርዓት ይታወቃሉም ነው የተባለው።

ግሪን ኸርት ሄሮ አዋርድ የሚል መጠሪያ ያለው ይህ ሽልማት፥ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቀነስ ለሚሰሩ አካላት ከህዝብ በሚሰጥ ጥቆማ መሰረት የሚሰጥ ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.