Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር 3 ሜዳሊያዎችን አገኘች

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግብፅ ካይሮ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ልዩ ኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያ 3 ሜዳሊያዎች አገኘች።

የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ስፖርተኞች የሚሳተፉበት የአፍሪካ የልዩ ኦሊምፒክ ውድድር በካይሮ በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ እና በቦሽያ ስፖርት እየተካሄደ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት በአራት አትሌቶች ተወክላለች።

ትናንት በተካሄደ የ100 ሜትር ሩጫ ውድድር በአትሌት ትግስት ኡጋሳ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በተጨማሪም በአትሌት ሚሊዮን ያደታ የብር እንዲሁም በአትሌት መዓዛ ኤልያስ የነሀስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች።

በውድድሩ እስካሁን 3 ሜዳሊያዎች ማግኘቷንም የኢትዮጵያ የልዩ ኦሊምፒክ ዳይሬክተር ዮናስ ገብረማርያም ለጣቢያችን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.