Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዋሽንግተን በሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር እንደማትሳተፍ ገለፀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በአሜሪካ ሊካሄድ የታሰበው ድርድር ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች።

የታላቁ የህዳሴ ግድብን የተመለከተ ውይይት በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል በአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ እና የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት በታዛቢነት የተገኙበት የሶስትዮሽ ድርድር በአሜሪካ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።

ሆኖም የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን በሃገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባላማጠናቀቁ የካቲት 19 እና 20 ቀን 2012 በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ ሊካሄድ በታሰበው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ እንደማይሳተፍ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በተጠቀሰው ጊዜ አሜሪካ በመገኘት ድርድሩን ማድረግ እንዳልታቻለ ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ቢሮ ማስታወቁንም ጠቅሷል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.