Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የተረጋገጠና አስተማማኝ የገበያ ዕድል እንድታገኝ ያደርጋታል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ከዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የተረጋገጠና አስተማማኝ የገበያ ዕድል ማግኘት እንድትችል እንደሚያደርጋት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ።
የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት እና የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና ድርድር ሂደት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
በወቅቱም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ግንኙነት እና ድርድር ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ልሳነወርቅ ጎርፉ ÷ ኢትዮጵያ ከዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የተረጋገጠና አስተማማኝ የገበያ ዕድል ማግኘት እንድትችል ያደርጋል ብለዋል፡፡
የድርጅቱን የግጭት መፍቻ ስርዓት በመጠቀም በተለይም የእርሻ ወጪ ንግዷ ኢ-ፍትሃዊ ባልሆኑ የውጭ ንግድ እንቅፋቶች በቀላሉ ጉዳት እንዳይደርስበት ለመካላከል እንደሚረዳም ተናግረዋል።
የህጎች ግልጽነትና አስተማማኝነት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ስላለው ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ንግድና ኢንቨስትመንት መስፋፋት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራልም ነው ያሉት።
ለዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ጠንካራ መልዕክት በማስተላለፍ የውጭ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ የሚያበረታታ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ልሳነወርቅ÷ በተለይም ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ሀገር በመሆኗ በወጪና ገቢ ንግድ ረገድ የትራንዚት መብቶችን እንድታገኝና ተጠቃሚ እድትሆን የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አያይዘውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዓለም ንግድ ድርጅት ምንነትና አባልነት የሚያሥገኛቸውን ጥቅሞች በአግባቡ ከመረዳትና ለሌሎች ከማስረዳት ጎን ለጎን መስራት የሚጠበቅበትንና ዘርፉ የሚጠይቀውን ሀገራዊ ተልዕኮ መወጣት ይገባዋልም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለው ድርድር ይሳካ ዘንድ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.