Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በድህረ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከሚጎበኙ ሰባት ሃገራት አንዷ ትሆናለች-ፎርብስ መፅሄት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥፋት በኋላ በጎብኚዎች ከሚመረጡ ሃገራት መካከል አንዷ እንደምትሆን ፎርብስ መፅሄት ተነበየ።

መፅሄቱ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የቱሪዝም ዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱን አስታውሷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ሃገራት በከፍተኛ ደረጃ ከዘርፉ የሚያገኙት ገቢ ማጣታቸውንም ነው በዘገባው ያመላከተው።

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥፋት በኋላም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት ሃገራት ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆኑ መፅሄቱ ትንበያ አስቀምጧል።

ኢትዮጵያም ባላት የተፈጥሮ ሃብት፣ ባህል እና ታሪክ፣ ቀዳሚዋ የጎብኚዎች መዳረሻ እንደምትሆንም ነው የተነበየው።

ዘገባው ኢትዮጵያን ቀደምት የሰው ዘር መገኛ፣ ቀደምት ስልጣኔ እና ቅኝ ገዢዎችን በጦርነት ያሸነፈች ብቸኛዋ አፍሪካዊት መሆኗንም ጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈም ውብ የሆኑ የተለያዩ ተፈጥሯዊ እይታዎች የታደለች መሆኗንም አንስቷል።

የኢትዮጵያውያን ባህል ብቻ የሆነውን እንጀራን በእጅ የመብላት ልምድም ሁሉም በህይዎቱ አንድ ጊዜ ሊሞክረው የሚገባ ብሎታል።

እነዚህና መሰል ምክንያቶችም ኢትዮጵያን የጎብኚዎች ተመራጭ መዳረሻ ያደርጓታልም ነው ያለው።

በመፅሄቱ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኢራን፣ ማይናማር፣ ጆርጂያ፣ ፊሊፒንስ፣ ስሎቬኒያ እና አፍሪካዊቷ ቱኒዚያ በኮሮና ማግስት የጎብኚዎች መዳረሻ ይሆናሉ ተብለው ተለይተዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.