Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በፈረንሳይ በሚካሄደው የቴክስ ዎርልድ የቴክስታይልና ጋርመንት ኤግዝቢሽን ላይ ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ ወር በፈረንሳይ በሚካሄደው የቴክስ ዎርልድ የቴክስታይልና ጋርመንት ኤግዝቢሽን ላይ እንደምትሳተፍ ተገለፀ፡፡

ኤግዝቢሽኑ በፈረንሳይ በፈረንጆቹ የፊታችን ሐምሌ 4 እስከ 6 ቀን እንደሚካሄድ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የተመረተ (“Made in Ethiopia” ) በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የሚገኙ 10 የአገር ውስጥ እና የውጪ አምራቾች በኤግዚብሽኑ የሚሳተፉ ሲሆን÷ የተለያዩ የመንግስት ሃላፊዎችም ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዓመት ሁለት ጊዜ በፈረንሳይ ፓሪስ በሚዘጋጃው በዚህ ኤግዚቢሽን ÷ ከዓለም አገራት የተወጣጡ የተለያዩ አምራቾች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል፡፡

የቴክስታይልና ጋርመንት ኤግዝቢሽኑ 1ሺህ 500 የሚጠጉ በዘርፉ የተሰማሩ አምራች እና ሸማቾችን በአንድ እንደሚያገናኝም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.