Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ2020 የገልፍ የምግብ እና መጠጥ ንግድ አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዱባይ እየተካሄደ ባለው የ2020 የገልፍ የምግብ እና መጠጥ ንግድ አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በዘርፍ የተሰማሩ 131 ላኪዎችም ዱባይ በሚገኘው የዓለም የንግድ ማዕከል በተዘጋጀው አውደ ርዕይ እየተካፈሉ ነው።

አውደ ርዕዩ እስከ ረቡዕ የሚቆይ ሲሆን፥ ከ98 ሺህ በላይ ጎብኚዎች እንዲሁም ከ5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ታድመውበታል።

አውደ ርዕዩ የምግብ እና የመጠጥ ኢንዱስትሪዎችን እና ባለሙያዎችን በአንድ ለማሰባሰብ ያግዛል ተብሏል።

በዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን ማስተዋወቅ አላማው ባደረገው አመታዊው ዝግጅት፥ አዳዲስ የዘርፉ ተዋናዮች እውቀትና ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል ሴሚናር ይዘጋጃል።

አውደ ርዕዩን የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዢ ሼክ መሀመድ ቢን ረሺድ አልመክቱም ከፍተውታል።

ምንጭ፡- 10times.com/gulf-food

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.