Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ ማዳበሪያ ለማምረት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ መንግስት ኩባንያ በአመት 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን ማዳበሪያ ለማምረት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን በኢፌዴሪ የፋይናንስ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ እና ኦሲፒ ኩባንያ ናቸው ፡፡
በድሬደዋ ነው የሚቋቋመው ፕሮጅክቱ በ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል።
በጀመሪያው ምዕራፍ 2 ነጠብ 5 ሚሊየን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ሲሆን በሁለተኛው ዙር 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን የማምረት አቅም እንዳለው ተነግሯል፡፡

በስምምነቱ መሰረት የአገር ውስጥ ሀብቶችን  በመጠቀም የኢትዮጵያ ጋዝ እና ሞሮኮ ፎስፎሪክ አሲድ  በድሬዳዋ የተቀናጀ የማዳበሪያ ማቀነባበሪያ ይቋቋማል።

በየጊዜው እያደገ የመጣውን የማዳበሪያ ፍላጎትን በዋናነት “ዩሪያ እና ኤን ፒ ኤስ+”  ለማሟላት ይህ ፕሮጀክት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይታመናል።

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ2022  ወደ አገር ውስጥ የምታስገባው ማዳበሪያ 1 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ሲሆን፥  ይህ ቁጥር በ2030 ደግሞ 2 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል።

ምንጭ፡- የፋይናንስ ሚኒስቴር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.