Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና የዴንማርኩ ዳንስኬ ባንክ ግሩፕ የ117 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና በዴንማርኩ ዳንስኬ ባንክ ግሩፕ መካከል የ117 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ እና የብድር ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የባንኩ ዳይሬክተር ጀልስፐር ፒተርሰን እና ምክትል ዳይሬክተሩ ኦላፍ ማርክ ሼት በበቪዲዮ ኮንፈረንስ በተዘጋጀ የፊርማ ስነ ስርአት ተፈራርመውታል።

ከዚህ ውስጥ 94 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮው የባንኩ ግሩፕ በድጋፍ መልክ የሚሰጠው ነው።

የድጋፍና ብድር ስምምነቱ ለአሰላ የንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሚውል ነው ተብሏል።

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ሲሆን 4 ነጥብ 49 ቢሊየን ብሩ ከባንኩ ግሩፕ በተገኘ ድጋፍ እና ብድር የሚሸፈን ይሆናል።

የዛሬው ስምምነት ዴንማርክ ለኢትዮጵያ የምታደርገው ድጋፍ አካል መሆኑም ተገልጿል።

የአሰላ ንፋስ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 100 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል ያመነጫል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.