Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 3 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ ዛሬ ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሃመድ አሊ ዩሱፍ ጋር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
 
የጅቡቲ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሃመድ አሊ ዩሱፍ በቲውተር ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ÷ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉ ጋር ዛሬ በጅቡቲ በኢትዮጵያና በሀገራቸው መካከል ስላለው መልካም ግንኙነት መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
 
ከዚያም ባለፈ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.