Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ አካላት ሃሳባቸው የተሳሳተ ነው-ቲቦር ናዢ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ አካላት ሃሳባቸው የተሳሳተ መሆኑን የቀድሞው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናዢ ገለጹ፡፡
 
ቲቦር ናዢ ጉዳዩን አስመልክተው በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ ኢትዮጵያ እንደ ዩጎዝላቪያ ትበተናለች የሚሉ አካላት ሀሳባቸው የተሳሳተ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
ዩጎዝላቪያ በአንደኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊዎች የተመሰረተች ሀገር መሆኗን ያስታወሱት ቲቦር ናዢ÷በአንጻሩ ኢትዮጵያ በርካታ ችግሮችን ያለፈች ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያ ረጅም ዘመን ያስቆጠረች ሀገር መሆኗን ነው የገለጹት፡፡
 
ኢትዮጵያ አሁን የገጠሟትን ፈተናዎች በድል ተወጥታ ሰላሟን እንደምታረጋግጥም ገልጸዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!ኢትዮጵያ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.