Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ጋር መጋቢት 15 በባህርዳር ስታዲየም ትጫወታለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማዳጋስካር አቻው ጋር መጋቢት 15 በባህርዳር ስታዲየም ይጫወታል፡፡

ቀደም ሲል ካፍ ጨዋታውን መጋቢት 18 እንዲካሄድ የወሰነ ቢሆንም ኢትዮጵያ ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት ወደ መጋቢት 15 መቀየሩን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ መጋቢት 21 ደግሞ በአቢጃን የኮትዲቫር አቻውን ይገጥማል፡፡

በመጀመሪያው ጨዋታ የቀናት ለውጥ የተደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ከማዳጋስካርና ከኮትዲቫር የሚያደርገው ጨዋታ ተቀራራቢነት ስላላቸው መሆኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.