Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከቁም እንስሳት ሀብቷ እየተጠቀመች አይደለም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ያላት ሀብት ሰፊ ቢሆንም የሚፈለገውን ያክል ውጤት ማግኘት ግን እንዳልተቻለ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በ2014 በጀት ዓመት በቁም እንስሳት 54 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ፥ 28 ሚሊየን ዶላር ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ በዘርፉ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ከቁም እንስሳት ላኪዎች ጋር እየተወያየ ነው፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የንግድ ትስስርና የወጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ፥ ዘርፉ የሚጠበቅበትን ያክል ለሀገር እየጠቀመ እንዳልሆነ አንስተው ችግሩን ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለመፍትሄው መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።

በዘርፉ በ2015 በጀት ዓመት 46 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት የታቀደ ቢሆንም ከታየው የሐምሌ ወር አፈጻጸም አንጻር ዕቅዱን ከማሳካት አንጻር ወደኋላ የቀረ መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል፡፡

ከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከልም ከጉሙሩክ ኮሚሽንና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በጋራ እየሰሩ መሆኑንም አቶ ካሳሁን ጎፌ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቁም እንስሳት ሀብት ከዓለም 10ኛ ከአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.