Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር የሚኖራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን ባስጠበቀ መልኩ ይቀጥላል – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር የሚኖራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ትብብርና የጋራ ተጠቃሚነትን ባስጠበቀ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

አምባሳደሩ የኢትዮጵያና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነት መርህን ባስጠበቀ መልኩ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በተለይ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተሳሳተ አረዳድና ትክክለኛ ያልሆነ አቋም እንደነበራቸው አስታውሰዋል።

አዲስ የሚመጣው የጆ ባይደን አስተዳደር ግን በአፍሪካ ዙሪያ መልካም እሳቤዎችን ይዞ ይመጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያም ከጆ ባይደን አስተዳደር ጋር የጋራ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ ትቀጥላለች ያሉት አምባሳደር ዲና፤ በኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ለአዲሱ አስተዳደር ግልፅ ለማድረግ ዝግጁ ነች ብለዋል።

በአሜሪካ የሪፓብሊካንና ዴሞክራት ፓርቲዎች የየራሳቸው የተለያዩ “ባህሪያት አሏቸው” እንዳሏቸው ያነሱት አምባሳደሩ ይህንንም ታሳቢ በማድረግ በቀጣይ የሁለቱን ሃገራት የጋራ ጥቅም በሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ በቂ ስራ እንደሚሰራ ነው ያነሱት።

በተለይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በህዳሴ ግድብና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ የነበራቸውን የተዛባ አመለካከት አንስተው ከባይደን አስተዳደር ጋር ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት የሚደረገውን የልማት እሳቤ በማስረዳት በቅርበት ይሰራል ነው ያሉት፡፡

አዲሱ የባይደን አስተዳደር ለኢትዮጵያም ብቻ ሳይሆን ከመላው አፍሪካ ጋር ጥሩ የትብብር መንፈስ እንደሚኖረው ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከጀመሩ ከ100 ዓመት በላይ አስቆጥረዋል፡፡

ኢትዮጵያና አሜሪካ ካላቸው የልማት ትብብር በተጨማሪ በሰላምና ደህንነት እንዲሁም ሽብርተኝነትን መዋጋት ላይ በጋራ ይሰራሉ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.